ባስሊዮስ ቲዩብ #BASLIYOS TUBE SUBSCRIBE channel logo ባስሊዮስ ቲዩብ #BASLIYOS TUBE SUBSCRIBE
  • Custom URL: @basliyostubesubscribe6640
  • Country: Sweden 🇸🇪

  • YouTube channel type
  • Audience: 3.56K
  • Video Views: 151.06K
  • # videos: 93
  • Estimated Earnings: $37 - $604
  • Category: Christian music Music Religion Society
  • Made For Kids
  • Date Created: 2020-05-12
  • Date Updated: 2024-05-31
Audience activity: 42
Views per video: 1.62K


#የቅዱሳን አባቶች ገድላቸውን ማህሌት የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኙበታል። ተወዳጆች ሆይ! ማለፍ መለወጥ በሌለባት በመንግሥተ ሰማያት ጸጋንና ክብርን እናገኝ ዘንድ በምግባር በትሩፋት እናጊጥ፡፡ በዚህ ዓለም የሚኖረን ውበትና ጌጥ ድንገት ታይቶ የሚጠፋ ነው፡፡ የማይቻል ቢኾንም ምንም በሽታ፣ ኀዘን፣ ብስጭት፣ ይህም የመሳሰለ ኹሉ ባያገኘን እንኳን የዚህ ዓለም ውበትና ጌጥ ሃያ ዓመት ነው፡፡ በወዲያኛው ዓለም የሚሰጠው የሚገኘው ክብር ግን በዝቶ ሲሰጥ ይኖራል እንጂ መቼም ቢኾን መች አያልፍም፡፡ አይለወጥም፡፡ እርጅና የለምና ቆዳው አይጨማደድም፡፡ ደዌ ሥጋ ደዌ ነፍስ አያገኘውም፡፡ ኀዘን አያወይበውም፡፡ በዚያ የምናገኘው ክብር፣ ውበት፣ ጌጥ ከዚህ ኹሉ የተለየ ነው፡፡ በዚህ ዓለም የምናገኘው ክብርና ውበት ግን የሚጠፋው ገና ከመምጣቱ ነው፡፡ ቢመጣ እንኳን አድናቂዎቹ ብዙ አይደሉም፡፡ ትሩፋትን ጌጥ ያደረጉ ሰዎች አያደንቁትም፡፡ የሚያደንቁት አመንዝሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ዓለም ከኾነው ክብር ልንለይ ይገባናል፡፡ መንግሥተ ሰማያትን እንወርስ ዘንድ ልንፈልገው የሚገባን ትሩፋትን ነው፡፡በዚህ ቻናል የቅድለ ቅዱሳንን የምንዘክርበት የምናስተዋውቅበት ነው የቅዱሳን በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን ኢትዮጵያን ከጥፋት ዘህቦችዋን ከስደት ይታደግልን #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"✞✞✞ (ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ)