WESEN SHO(ወሰን ሾዉ channel logo WESEN SHO(ወሰን ሾዉ
  • Custom URL: @wesenshowu6
  • Country: United Kingdom 🇬🇧
  • Language: English

  • YouTube channel type
  • Audience: 3.64K
  • Video Views: 35.97K
  • # videos: 133
  • Category: Religion Society
  • Date Created: 2022-03-11
  • Date Updated: 2024-06-27
Audience activity: 9
Views per video: 270
Keywords: @ELSA TUBE ኤልሳ ዩቱብ 200 ሁለገብ ቻናል


#ወርቃማ.ብቁ ሀሳቦች. #ፍቅር ቤቱን የሠራበት ልብ እንዴት የታደለ ነው? ምክንያቱም ከዓለም ጭንቀት ሁሉ መዳኛው ፍቅር ነውና። ፍቅር ትዕግስትና ማመዛዘንን ወደ ምንምነት የሚቀይራቸው የነጐድጓድ ኃይል ነው። አፍቃሪ ስለራሱ ደህንነት ማሰብ አያውቅበትም፤ የትችት ተራራ ለእሱ ከገለባ ክምር የቀለለ ነው።እንዲያውም ትችት የፍቅሩን ኃያልነትየሚጨምርለትጉልበቱይሆናል#ዓለምበሙሉዕብድነውይለኛል።በእርግጥም ዕብድ ነኝ። አናንተም ደግሞ ዕብድ ናችሁ። ዓለም በሙሉ ዕብድ ነው። ለመሆኑ ዕብድ ያልሆነስ ማን ነው? ይሁንና እነዚህ ዕብዶች ደግሞ እኔን ዕብድ በማለት ይጠሩኛል። ከእነሱአንዳንዶቹለስማቸውናለክብራቸውያበዱናቸው።አንዳንዶቹገንዘብበመከተል አብደዋል። ሌሎቹ ደግሞ ሥጋን ውበትን እየተከተሉ ያብዳሉ። እሱ ፈጣሪውን ተከትሎ ያበደ ግን በእርግጥም የተባረከ ነው። እኔ እንዲህ ዓይነቱ ዕብድ ነኝ#የሰው ልጅ ምኞት ገደብ የለሽ ነው። ምኞት በጥም የተቃጠለ ሰው የሚጠጣው ጨዋማ ውሃ ነው፤ ጨዋማ ውሃ የውሃ ጥምን አለማርካት ብቻ ሳይሆን ጥሙ እየጨመረ እንዲሄድ ማድረጉ የማይቀር ነውና። ስለዚህም የሰው ልጅ የእርካታ ምንጩ ከውስጡ ነው፤ በምኞቱ ግን አለመርካታ ብቻ ሳይሆን ስቃዩም እየጨመረ ይሄዳል። እናም ለምኞትህ ገደብ አበጅለት#አብዛኛው የሰው ልጅ የሚከተላቸው እምነቶችና በእምነቱ ውስጥ የሚፈፅማቸው ድርጊቶች መነሻቸው ልማድ ነው። እምነት በዕውቀት መገለጥን ካልያዘ የሚጠይቀውም ሆነ ምላየሚያገኝለት ጥያቄ ስለማይኖር ሌላ ስለሚያደርጉት ብቻየሚደረግከንቱተግባርሆይይቀራል#ፍቅር በውስጥህቦታንሲያገኝየውበት መገለጫውትሆናለህ። ፍቅር የያዘው ሰው የሚንፀባረቅበት መስተዋት ነው። ምክንያቱምውበትምሆነነፀብራቁመነሻቸውፍቅርነውናየሁለቱም ምንጭ ፍቅር ነው $ኤልሳ #ዩቱብ #ELSA TUBE ✍️