Mahibere Kidusan channel logo Mahibere Kidusan
  • Custom URL: @eotcmk
  • Country: United States 🇺🇸

  • YouTube channel type
  • Audience: 465K
  • Video Views: 64.14M
  • # videos: 10,345
  • Estimated Earnings: $16.04K - $256.56K
  • Category: Religion Society
  • Global Rank: 129315
  • Country Rank: 23006
  • Date Created: 2009-12-15
  • Date Updated: 2024-07-02
Audience activity: 137
Views per video: 6.2K
Audience growth speed: 87
Keywords: Mahibere Kidusan EOTC Ethiopia Tewahedo Orthodox MK spiritual Menfesawi MKTV Mezmure


ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አመሠረራት ጥቂት ነጥቦችን እናስታውስ፡፡ በ1980ዎቹ የጋንቤላና የመተከል የሠፈራ ዘመቻ ጥቂቶቹን አገናኘ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ሌሎችን በጥበቡ እየጠራ በክረምት ጊዜ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ሲዘጉ በዝዋይ ገዳም እንዲገናኙ አደረገ፡፡ በመጨረሻም አብዛኛዎቹን ወጣቶች በ1983 ዓ.ም በብላቴ ካምፕ አገናኛቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ መልካም አጋጣሚዎች ሆኑላቸውና የተለያዩ ማኅበራትን እያቋቋሙ ወጣቱ ትውልድ ከቤተ ክርስቲያን ጋር የማስተዋወቁን ሥራ አፋፍመው ቀጠሉበት፡፡ በዚህ የተሰበሰበው ኃይል አሁንም ተደራጅቶ ጠንካራ አገልግሎት የሚሰጥበትን አንድ ማኅበር እየፈለገ መጣ፡፡ በዚህ ምክንያት የተለያዩ ማኅበራትን በመመሥረት የየአቅማቸውን አገልግሎቶች ሲፈጽሙ የቆዩት ወጣቶች በአንድ ማኅበር ቢሰባሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገነዘበ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር በመላእክት ስም፣ በእመቤታችን ስም፣ በቅዱሳን ስም የተሰበሰቡት ሁሉ ለመታሰቢያነት የሚጠሯቸውን ቅዱሳን የማያስቀርና ተልእኮአቸውን የማይለውጥ አንድ ማኅበር ለመመሥረት የወሰኑት፤ ወስነውም አልቀሩ መሠረቱት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፡፡ ውኃ ልትቀዳ ወርዳ ጌታችንን አግኝታ እንደተመለሰችው ሰማርያይቱ ሴት፤ ከሄዱበት ምድራዊ ዓላማ ተጨማሪ ሰማያዊ ዓላማን አንግበው መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጥ ማኅበር ለመመሥረት ምክንያት የሆኑት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እንደሙያ ዝግጅታቸውና ስጦታቸው ቤተ ክርስቲያናቸውን ለማገልገል አደራ ተቀበሉ፡፡ /ዮሐ. 4፤7/ ስለዚህም ማኅበሩ ሐዋርያዊ ተልእኮን ለማስፋፋትና ግቦቿን አሳክታ ከችግሮቿ ወጥታ ለሕዝቦቿ ማኅበራዊ ሕይወት ለውጥ የመሪነት ሚና የምትጫወት ቤተ ክርስቲያንን ለማየት የሚያስችል የአገልግሎት ስልት ነድፎ ብቅ አለ፡፡