Azi Toub channel logo Azi Toub
  • Custom URL: @azitoub3867

  • YouTube channel type
  • Audience: 514
  • Video Views: 2.52K
  • # videos: 33
  • Date Created: 2020-05-31
  • Date Updated: 2024-04-28
Audience activity: 4
Views per video: 76


ዛሬ አበባ ተሰጠኝ፣ ልደቴ ወይም የተለየ ቀን ሆኖ አደለም፣ ትላንት ማታ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጨቃጨቀን ነበር ፣ ብዙ ስሜቴን የሚጎዱ ቃላቶች ተናግሮኝ ነበር ነገር ግን ያደረገው ተሰምቶት አበባ ስለሰጠኝ ይቅር አልኩት። ዛሬ አበባ ተሰጠኝ፣ ፍቅር የጀመርንበት ቀን ስለሆነ አሊያም የተለየ ቀን ሆኖ አደለም። ትላንት ማታ ከግርግዳ ጋር አጋጨኝ፣ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ አነቀኝ፣ የሆነ ቅዥት ይመስላል፣ እውነት አልመስልሽ አለኝ። ዛሬ ጠዋት ከዕንቅልፌ ስነቃ ሰውነቴ በህመም ቆስሎ እና ሰምበር፣ በሰምበር ሆኜ ነበር። ባረገው ነገር ሳይፀፀት አልቀረም መሰለኝ አበባ ሰጠኝ። ዛሬ አበባ ተሰጠኝ የእናቶች ቀን ወይም የተለየ ቀን ሆኖ አደለም፣ ትላንት ማታ በድጋሚ መታኝ፣ ከምንም ጊዜ በላይ የከፋ ድብደባ አደረገብኝ፣ እሱን ትቼው ከሄድኩ ምን አደርጋለሁ? ሌጆቼን እንዴት ነው የማሳድገው? ገንዘብስ ኬት አመጣለሁ? እሱን ፈርቼዋለሁ? እሱንም ትቶ መውጣት ፈርቻለሁ። ነገር ግን ባደረገው ነገር ሳያፍር አልቀረም አበባ ሰጠኝ። ዛሬ አበባ ተሰጠኝ፣ የዛሬው ቀን ልዮ ቀን ነች። ዛሬ ቀብሬ የሚፈፀምበት ቀን ነው። ትናንትና ማታ ገደለኝ። ነፍሴ እስክወጣ በአሰቃቂ ሁኔታ ቀጥቅጦ ገደለኝ። በውስጤ እሱን ጥሎ የመውጣት ብርታት እና ጥንካሬ ቢኖረኝ ኖሮ፣ ዛሬ አበባ አይሰጠኝም ነበር።