Biku Media ብቁ ሚዲያ channel logo Biku Media ብቁ ሚዲያ
  • Custom URL: @bikumedia8190
  • Country: United States 🇺🇸

  • YouTube channel type
  • Audience: 2.12K
  • Video Views: 0
  • # videos: 0
  • Category: Entertainment Society
  • Date Created: 2020-03-24
  • Date Updated: 2024-07-08
Keywords: Ethiopia ethiopian amharic addis ababa Ethiopian Ethiopian News Ethiopian News Today Amharic News Ethiopian Comedy Ethiopian Movie Ethiopian Music Amharic Drama Ebs Seifu on ebs DireTube


ብቁ ሚዲያ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኪነጥበባዊ በተለይ ደግሞ አገራዊ እሳቤዎች ላይ ከግለሰብ፣ ህብረተብ፣ ማህበረሰብ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የአመለካከት፣ አስተሳሰብ፣ እይታ፣ አረዳድ፣ ውሳኔ እና ድርጊት የበቃ፣ የሰለጠነ፣ የሚያራምድ እና የሚያሻግር እንዲሆን በአስተሳሰብ ጥልቀትን፣ በአመለካከት ሚዛናዊነትን፣ በእይታ ሰፊነትን፣ በውሳኔ አስተዋይነትን እንዲሁም በድርጊት ደግሞ ሀላፊነት የተሞላበት እንዲሆን የሚረዱ ዝግጅቶችን የሚያቀርብ ሚዲያ ነው። ብቁ ሚዲያ አላማና ግቡን በተለየ መልኩ ብሄራዊ አንድነታችንን የሚያጠናክሩ፣ መልካምና ጥሩ አገራዊ እሴቶቻችንን የሚያጎለብቱ፣ ማህበራዊ አብሮነታችንን የሚያበረቱ፣ ዘላቂ የአገራችንን ሰላም፣ ማህበራዊ እሴቶች፣ ኢኮኖሚያዊ እድገቶች፣ በሳልና ገንቢ ኪነጥበባዊ እይታዎች እንዲሁም የሰለጠነ የፖለቲካ አረዳዶችን የሚያግዙና ጠቋሚ ዝግጅቶች ላይ የሚሰራ ሚዲያ ነው። የበለለፀገ እና ሰላማዊ አገር ለማስቀጠል የበቃና የነቃ ማህበረሰብን፣ የበቃና የነቃ ማህበረሰብን ለመገንባት ደግሞ የበቃና የሰለጠነ ህብረተሰብን መፍጠር ያለብን ሲሆን ህብረተሰብ የግለሰብ ስብስብ በመሆኑ የበቃና የሰለጠነን ግለሰብን አንድ ብለን መጀመር አለብን። የበቃና የነቃ ግለሰብን ለመፍጠር የአንድ ሰው ወይንም የአንድ ግለሰብ መገለጫው አመለካከቱ፣ አስተሳሰቡ፣ እይታው፣ አረዳዱ፣ ውሳኔውና ተግባሩ በመሆኑ በእያንዳንዱ ሰው፣ ግለሰብ እንዲሁም ዜጋ ላይ የበቃና የነቃ አስተሳሰብ እና አስተዋይና ቀና አመለካከት፣ ከፅንፍ የራቀና ሚዛናዊ አረዳድ፣ የሚያራምድ፣ የሰፋና ጠባብ ያልሆነ እይታ እንዲኖረው የሚያግዙ ዝግጅቶችን ብቁ ሚዲያ ያቀርባል። "በነገሮች ሁሉ ብቁ እንሁን፤ በነገሮች ሁሉ እንብቃ" የሚዲያችን መልክት ነው።