ደጀ ሰላም // Deje Selam channel logo ደጀ ሰላም // Deje Selam
  • Custom URL: @dejeselam8707
  • Country: United States 🇺🇸

  • YouTube channel type
  • Audience: 3.95K
  • Video Views: 160.73K
  • # videos: 29
  • Estimated Earnings: $40 - $640
  • Category: Religion Society
  • Date Created: 2019-10-12
  • Date Updated: 2024-06-24
Audience activity: 40
Views per video: 5.54K
Keywords: Ethiopian Orthodox Tewahedo


በስመ አብ ፥ ወወልድ ፥ ወመንፈስ ቅዱስ ፥ አሀዱ አምላክ አሜን። እንኳን ወደ "ደጀ ሰላም " ዩቲዩብ ቻናል በሰላም መጣችሁ። ይህ ቻናል የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሆኑ የፊልም እና ተያያዥ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሲሆን ፤ ባላቸው የኪነጥበብ ክህሎት በመጠቀም ክርስቲያናዊ ሀሳቦችን ፣ ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች እና ልናውቃቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እንደማንኛውም አለማዊ አጀንዳ በድራማ ፣ በዶክመንተሪ ፣ በቃለመጠይቅ ፣ በውይይት እና በፊቸር ፊልም ሰርተው ሊያቀርቡበት ያዘጋጁት ሚዲያ ነው። እኛ (የዚህ ሚዲያ አዘጋጆች) የኢ/ኦ/ተ/ቤ ምዕመናን እንጂ አገልጋዮች ሳንሆን ፤ በዚህም ቻናል በሙያችን በመታገዝ ከሌሎች መንፈሳዊ ሚዲያዎች ለየት ባለ አቀራረብ እንደማንኛውም ምዕመን ያልገቡንን ጥያቄዎች ወይም ልንማር እና ልንረዳ የሚገቡንን ዝርዝር ጉዳዮች የቅድስት ቤተክርስቲያን አገልጋዮችን በማቅረብ እና የሚያስተምሩበትን መድረክ በመፍጠር ፤ ልክ እንደኛ በዓለም ወጥመድ እየወደቀ እየተነሳ ላለ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሻተ ልብ ላለው እና ከኃጢአት ነፅቶ ወደ ቀጥተኛዋ መንገድ ተመልሶ እግዚአብሔርን መቅረብ ይችል ዘንድ ለእርሱ በሚስማማ መንገድ በሙያችን ሰርተን እያቀረብን አብረን እንማራለን። ስለዚህ በዚህ ቻናል የሚሰሩ የሚዲያ ስራዎች አቀራረባቸው በሚታየው መልኩ እንዲሆን የተደረገው በባለሙያዎቹ እውቀት ፣ የረጅም ጊዜ የሚዲያ ልምድና ፍላጎት ላይ ተመስርቶ እንጂ አቀራረቡ ፈፅሞ ቅድስት ቤተክርስቲያንን አይወክልም። ነገር ግን የሚቀርቡት ዝግጅቶች ላይ የሚነሱ ሀሳቦች በሙሉ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንዲት ሰንዝር ወደቀኝም ወደግራም አይወጡም ! ፨ወስብሐት ለእግዚአብሔር፥ወለወላዲቱ ድንግል፥ወለመስቀሉ ክቡር፨