አቡቀለምሲስ ማለት ረአየ ኅቡኣት አበ ራዕይ አበ ትንቢት ማለት ሲሆን የተሰወረውን የተደበቀውን የተከደነውን የሚገልጥ ማለት ነው። መሠራታዊ ዓለማው በሀገረ ስብከታችን ብሎም በመላ ቤተ ክርስቲያናችን የተሰወሩ ገዳማትን የተደበቁ ሊቃውንትን የተከደኑ ታሪኮችን የተሸሸጉ ቅርሶችን ማውጣት እና የተንሸዋረረ ታሪክ ማስተካከልና የጎበጠውን አዲሱን ትውልድ ማነጽ ነው