ZERAYONAS / ዘርዓዮናስ channel logo ZERAYONAS / ዘርዓዮናስ
  • Custom URL: @zerayonas3870
  • Country: United States 🇺🇸
  • Language: English

  • YouTube channel type
  • Audience: 14
  • Video Views: 0
  • # videos: 0
  • Date Created: 2019-11-08
  • Date Updated: 2024-04-05
Keywords: ZERAYONAS AKLILU ZERAYONAS YONAS AKLILU YONAS yonas aklilu alemu diakon yonas aklilu zerayonas aklilu diakon diakon yonas yoni yo ethiopia yonas ethiopia


ዘርዓዮናስ® በማንመለከተው የኢትዮጵያ ገፅታ ውስጥ ብዙ ሺህ የበቁ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ትንሳኤ በተጠንቀቅ ቆመዋል:: እነኝህ ኢትዮጵያውያን ከቅዱሳን መላእክቶች ጋር ህብረት የፈጠሩ የብርሀን ዝናር የታጠቁ ሀይላት ናቸው:: የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ላይ የሚያፀኑ የቀደሙት አያቶቻቸው ልጆች ናቸው:: እነኝህ ኢትዮጵያውያን የእሳት ሰይፍ የታጠቁም ናቸው:: ምድርን ያቆሻሹ ከሳጥናኤል ያበሩ የክፍት ተግዳሮቶችን ያፀዳሉ:: ቅዱስ ሚካኤልም ይራዳቸዋል:: ይመራቸዋል:: እነኝህ ኢትዮጵያውያን ጥበብን ከአርያም የሚቀዱ ናቸው:: ቅዱስ ዑራኤልም ያራዳቸዋል:: ይመራቸዋልም:: በዛ የኢትዮጵያ ገፅታ ያሉት ኢትዮጵያውያን ምድርን ከሰማይ የሚያገናኝ መሪ አላቸው:: የአባቱን የአዳምን ከአርያም የወረደ ጳዝዮን የደፋ በእጁ ቀጭን ዘንግ የያዘ:: ይህች ዘንግ የዓለምን የሀይል ሚዛን የምትቀለብስ ታላቅ ምስጢር ያዘለች ነች:: ይህ መሪ የፍጥረታትን ልሳን ሁሉ የሚያውቅና የሚናገር እነርሱን ማዘዝም የሚችል ነው:: ይህች የማናያት ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ውስጥ ከመሬት በታችና ከመሬት በላይ ብትመሽግም መገለጫዋ ግን ቅርብ ነው:: ያኔ ስትገለጥ አገሬ በተራራ ላይ የተከተመች ብርሃናዊ ከተማ ትሆናለች:: ዓለም በተራራው ላይ የሚንቦገቦገውን ብርሀን እያየ ይመጣል:: በብርሃኑም ዓለም ይድናል::